፨ የጌታው ፡ ሸህ ሁሴን ጅብሪል ፍርድ ፣ መደድና ተውሂድ ፣ ከትክክለኛው በአደም ከተጻፈው ፡ አረበኛው ወደ አማረኛ ፡ የተገለበጠ ነው። ተመጀመሪያው ታአጀሙ ጋር እያመሳከርክ ፡ አጀም ማንበብ የምትችል ተሆነ ፡ የምታነበው ፍርድ እነሆ ይሄውልህ። አጀሙንም አሁን በቅርብ ጊዜ ፡ ፈጣሪ ተፈቀደ በገበያ ላይ ይውላል።
 
 
     የጸሀፊው ታደሰ አስናቀ ፡ ለጌታው ለሽህ ሁሴን ጅብሪል ፡ ያለው ዝምድና ፡ ተዚህ እንደሚከተለው ነው።  
      ፨ የትውልድ ዘር አመጣጥ።  
     ታደሰ አስናቀ/ባየ  
     እንድሪስ ሐሰን/የኪታብ ስም ኡስማን  
      ፨ እንድሪስ ሐሰን ፡ ለሽህ ሁሴን ፡ አራተኛው የልጅ ልጅ ሲሆን ፡ ጌታው ሸህ ሁሴን ጅብሪል ፡ ማንን ወለዱ ፡ እንደዚህ ይቀጥላል ማለት ነው።  
     ራህመት ሁሴን ፡ የሽህ ሁሴን ጅብሪል ልጅ ናት።  
     በየነች ወለላው ፡ የረህመት ሁሴን ልጅ ናት።  
     ጀሚላ አህመድ ፡ የበየነች ወለላው ፡ ልጅ ናት ፡ የታደሰ አስናቀ እናት ማለት ነው።  
     ታደሰ አስናቀ/ባየ እንድሪስ ሐሰን/አሊ ኡስማን እንድሪስ ሐሰን አሊ  
     የኪታብ ስም ፡ በእስልምና ሁልጊዜም ሙስሊሞች አለን።  
 
      ፨ ታገር ቤት የወጣሁት ፡ በደርግ ጊዜ ነው፣ አሁን ይምኖረው በካናዳ ውስጥ ፡ ቶሮንቶ ተሚባል ከተማ ነው። ካናዳ ውስጥ 33 ዓመት አለኝ። ታንዲት ሴት ፡ ሶስት ልጆች አሉኝ ፣ እናታቸው እንዳላያቸው ስለከለከለችኝ ፡ 23 ዓምት ፡ አይቻቸው አላቅም። ስንት ጊዜ በጓደኞች አማካይነት ፡ ለማየት ሞከርኩኝ ፣ ቢሆንም እናታቸው ፈቃደኛ አልሆነችም ፣ እኔን የጎዳሁት መስሏት ፡ እነሱንም አባታቸውን እንዳያዩ ፡ ለ23 ዓመታት ፡ ከልክላቸው ትኖራለች ፣ ይሄን ይመስላል የኛ ኑሮ ፡ ባገር ቤት የሚኖር ሰው ፡ የሚቀናበት።
 
      ፨ አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ ፣ ሁለት ጓደኛሞች ተሻርከው አንድት ፡ አበባ ይተክላሉ ፡ አበባዋም ቦታው ስለተመቻት ፡ በጣም እያደገች ስትመጣ ፡ ሁለቱም ጧት ማታ ፡ ሲገቡ ሲወጡ ያዩአታል ፣ ተለታት አንድ ቀን ፡ ሁለቱ ጓደኛሞች ይጣላሉ ፣ አንደኛው ለሊት ይነሳና ፡ ጓደኛውን የጎዳሁ መስሎት ፡ አበባዋን ነቅሎ ጣላት ፤ ጓደኛውም ማን እንደነቀላት ስላላወቀ ፡ ጧት ተበራፉ ላይ ፡ ቆሞ እየተመለከተ ፡ የነቀላት ጓደኛው ብቅ ይልና ፡ እንዳታያት ብየ ፡ እኔ ነኝ የነቀልኳት ብሎ ፡ ገና ሳይጠይቀው ይነግረዋል ፣ እኔ እንዳላያት ፡ ብለህ ነው ፡ የነቀልካት አንተስ ታያታለህ ወይ? ብሉ ጠየቅው ይባላል ፣ ነቃዩም ይህ ለኔ አልዞረልኝም ነበር ፡ ይሄም አለ ለካ ፡ አለው ይባላል።
 
 
     taddesseasnake@gmail.com
 
             ***