...አደራ ብያለሁ ፡ ደግሜ ደግሜ ተመሄደ በፊት ፡ በሞት ተቀድሜ... ...ሁሴን ስጠኝ ብለህ ፡ አትምጣ አጠገቤ ሰጩም ነሹም አላህ ፡ ልንገርህ ተልቤ... ...እስቲ አላህን ፍራ ፡ አታጎንብስ ለኔ ለሰው እንዳሰግዱ ፡ ረግሚያለሁ እኔ...
በኢትዮጵያ ውስጥ ፡ ለወልዮች ተመቃብራቸው ላይ ፡ ፍየል ይታረዳል ፡ ሰው ይነዘርባቸዋል ፡ ሞተውም ልክ በሂወት እንዳሉ ፡ ሰው ጀባታ የሰጣቸዋል ፣ እኔም ካያታቸን ፡ ሽህ ሁሴን ጅብሪል ዘንድ ፡ ወሎ ሄጄ ፡ ባይኔ ያየሁት ፡ ነገር ነው። እሳቸው ግን ፡ ከመሞታቸው በፊት ፡ ይሄን እንዳታረጉ ፡ ብለውን ሄደዋል። ሕዝባችን ግን ፡ በዚህ አይስማማም ፣ እንዳውም ይሄንን ተተቃወምክ ፡ ሊጣሉህም ይችላሉ ፣ ጌታው ሸህ ሁሴን ጅብሪል ፡ በማነኛውም በሞተ ሰው ፡ እንዳትመጀኑ ሲሉ አስጠንቅቀዋል ፣ እንዳውም ከዘመዶቻችን ፡ አንዱን ሰው ፡ እኔም ሙክት ፡ ገዝቸ ስለነበር ፡ ለምን ለሳቸው ብለን ፡ ሶደቃ ነይተን ፡ ብናርደውና ቢበላ ፡ ምን አለው? ብየ ብጠይቀው ፡ ቤተሰቡ እንዳይሰማህ ፡ ነው ያለኝ ፣ ታዳ ሰው ከዚህ ድረስ ፡ የሚመጣው ለሳቸው ፡ ጀባ ሊል ነው ፡ እንጅ እኛን ለማየት ምስሎህ ፡ ነው እንዴ : አለኝ። ያው እሱ ባለው መንገድ ታረደ ማለት ነው።
አደራ ብያለሁ ፡ ደግሜ ደግሜ ተመሄደ በፊት ፡ በሞት ተቀድሜ አፌ ሳይያያዝ ፡ ታምሜ ደክሜ አፈር ሳይጫነኝ ፡ ሳይረሳ ስሜ ለናንተም ይበጃል ፡ ለኔም ያነው ጥቅሜ የማስቀምጠው ስንቅ ፡ ላአኺራ ቀለቤ ታላህ ፊት ስጠራ ፡ ስጠየቅ ቀርቤ እንዳልደናገር ፡ እንዳይፈራ ልቤ በናንተ ዱኣ ላይ ፡ የኔንም ደርቤ አላህን ስለምን ፡ ስጣራ አሻቅቤ ተመቃብሬ ውስጥ ፡ ተኝቸ አሽልቤ መቃብሬ ዙሪያው ፡ በሰው ተከብቤ ተደፍቶ ሲያለቅስ ፡ አየሁት ቀርቤ አፌ ባይናገር ፡ አዘንኩኝ በልቤ እኔ ምን ሀብት አለኝ ፡ ያኖርኩት ቆጥቤ? ለሰው የምሰጠው ፡ ለራሴ ጠግቤ ትችው ሄድኩኝ አይደል ፡ መች ወሰድኩ ቀንጥቤ ሰው ስለሆንኩ አይደል ፡ ጨንቆኝ ተጠብቤ ስተቱን ልንገርህ ፡ አንድ ባንድ አስቤ ሁሴን ስጠኝ ብለህ ፡ አትምጣ አጠገቤ ሰጩም ነሹም አላህ ፡ ልንገርህ ተልቤ ተየት አምጥቸ ነው ፡ የመሰጥህ እኔ? አላህ ሰጥቶኝ አይደል ፡ እኔስ መለመኔ ስጦታው የሚያጠግብ ፡ ያአላህ ነው ወገኔ ሰውማ ስው አይደል ፡ ያንተ ቢጤ እንደኔ እያለው የሚነፍግ ፡ ጨካኝ አረመኔ ወልይ የለም ብየ ፡ አይደለም እኮ እኔ የዝህ አይነት ስልጣን ፡ አይገባም ለኔ እኔ እኮ ሙቻለሁ ፡ አልቆብኝ ዘመኔ ተሞተኩኝ በሁዋላ ፡ ያው አምዋት ነው ጅስሜ አላህን ለምነው ፡ አትሁን ቦዘኔ አላህኮ ሲሰጥ ፡ ማዝያ አይልም ሰኔ ቀጠሮም አይፈልግ ፡ ሰኞና ቅዳሜ ውሽት እንዳይመስልህ ፡ ነገርኩህ ብውኔ እያረገላችው ፡ እያየሁት ባይኔ እኔ አንድ ለማኝ ነኝ ፡ ታንተ አልበልጥም እኔ ሁሴን ብለህ ጠርተህ ፡ አትለመን በስሜ እንዳይቆጣ አላህ ፡ አዳምጠኝ ወንድሜ ናና ዱአ እናድርግ ፡ ቁጭ በእል ታጠገቤ አላህ ይሰጠናል ፡ መጀን በል በነቢ ዱአ ጠቃሚ ነው ፡ ላንተም ሆነ ለኔ እኔ የምለምነው ፡ አላህን ነው ቁሜ በጤናየም ብሆን ፡ ታምሜም ደክሜ ቢሰጠኝ መርሃባ ፡ ተደስቶ ቀልቤ ባጣም አመስግኘ ፡ ቸግሮኝ ተርቤ ሰጩ እሱ ነውና ፡ ሀብትም ቢሆን እድሜ በሽታም ቢይዘኝ ፡ እሱ ነው ሀኪሜ እሱ ነው አዛዡ ፡ በስጋ በደሜ ነብዩም ብለዋል ፡ አደራ ኡመሜ ታላህ ያራርቃል ፡ ያመጣል ኩነኔ ሱጁድና ሶላት ፡ ላአላህ ነው ወገኔ ብለው ተናግረዋል ፡ የጦይባው ምስለኔ እስቲ አላህን ፍራ ፡ አታጎንብስ ለኔ ነቢ ከልክለውት ፡ ማን ፈቀደ ለኔ ለሰው እንዳሰግዱ ፡ ረግሚያለሁ እኔ ለሞተም ተቀብሮ ፡ ላለም ገና በድሜ አቤት ብለህ ስማ ፡ ትዛዙን እንደኔ ትዛዙን ተቀበል ፡ አትበል ለምኔ እንዳረሳው ብየ ፡ ተሸክሜ አንግቤ ለሰው እያስረዳሁ ፡ ልንገርው አንብቤ አላሀን መፍራት ነው ፡ ይህ ነው ጥበቤ እኔም ተደስቸ ፡ ሌላም ሰው ጠቅሜ እሞክራልሁኝ ፡ በምችለው አቅሜ ተዛ ወዳ አላልፍም ፡ ይህ ነው ደንበሬ ተናግሬያለሁኝ ፡ ውርድ ተራሴ እኔ። ***