...ሌላው አማኝ ተውጭ ፡ ሙስሊሙን ሲያየው
ድንጋዩን ይመስላል ፡ የምንገዛው
እንዳትፈርዱበት ፡ ሰው ስላልገባው...
ሙስሊሞች ፡ ወደ መካ ለሃጅ ይሄዳሉ ፣ ክርስቲያኖች ወደ እይሩሳሌም ይሄዳሉ ፣ አንዳንዱ ክርስቲያን ፡ መካ ማለት ፡ ምን እንደሆነ አይግባውም ፣ እንዳው ሙስሊሙ ፡ የሆነ ደንጋይ ተሳልሞ ፡ የሚመለስ ነው ፡ ይሚመስለው ፣ ጌታው ሸህ ሁሴን ጅብሪል ፡ ስለ መካ ምንነትና ታሪክ ፡ ባጭሩ እንድህ ሲሉ አስቀምጠውታል።
እስልምናን ማውራት ፡ ማስረዳት ለስው
ቡዙ አያስቸግርም ፡ ሰው እንድገባው
በዟሂር ላየው ሰው ፡ መካ ደንጋይ ነው
ውስጡን ግን የሚያውቀው ፡ ያው ኻሊቁ ነው
ሌላው አማኝ ተውጭ ፡ ሙስሊሙን ሲያየው
ድንጋዩን ይመስላል ፡ የምንገዛው
እንዳትፈርዱበት ፡ ሰው ስላልገባው
የመጀመሪያው ቤት ፡ ላዐላህ መገዣው
የሰው ልጅ ታዐላህ ጋር ፡ የሚያገናኘው
አምስት ወቅት ሶላት ፡ ምስገጃ ቂብላው
ነቢ ኢብራሂምም ፡ አንድ ጊዜ ሰራው
ልጁ አብሮ እይረዳው ፡ እያቀበለው
ቡዙ ጊዜ ጠፍቷል ፡ ጎርፍ እየመታው
ጣኦት መደርደሪያ ፡ ቁረይሾች አርገው
ሰው ይገዛው ነበር ፡ እንደ ፈጣሪው
ነቢዩ ሙሐመድ ፡ ሰባብሮ ጣለው
ነቢ ሙሐመድም ፡ ሰርቷል እንደዛው
ገንዘብ ባያዋጣም ፡ ሀብትም ባይኖረው
በጉልበት እረድቷል ፡ ሲሰቀል ጣራው
ቁረይሾች ተጣልተው ፡ ነበር ተናንቀው
አንድ መላ አመጡ ፡ እንደፋል አርገው
ተውስጥ ቁጭ ብለው ፡ ነበር ተፋጠው
የመጀመሪያው ሰው ፡ በበር የሚገባው
በሚለው ሊስማሙ ፡ እሱ በሚያዘው
ሙሐመድ ብቅ አሉ ፡ ተወዳጁ ሰው
ገና ነቢ ሳይሆን ፡ ጌታ ሳይሾመው
እንኳን መጣህልን ፡ አብረን እንስራው
ዙሪያውን ያዙ አሉ ፡ ሽቅብ እናንሳው
አንስተው ሰቀሉት ፡ ባንድላይ ሆነው
የመካ ታሪኩ ፡ ባጭሩ ይህ ነው።
***