ዩሐንስ ተመታ ፡ ስልጣኑን ተቀማ ጭልጋ ጎንደር ገባ ፡ የድርቡሽ ዑለማ ቤተክርስቴያኖች ፡ ነደዱ እነደ ሻማ እለፈልፋለሁ ፡ ታለ የሚሰማ ቡዙ ቄስ አየሁኝ ፡ መስቀሉን ሲቀማ መስጊድ ገብቶ ሲሰግድ ፡ ሶላት በጀምአ
አገራችን ኢትዮጵያ ፡ የክርስትናና የሙስሊም ሀይማኖት ተከታይ ፡ ሕዝቦች እንደሚኖሩባት ፡ ለሁላችንም ግልጽ ነው ፣ ያሁኑን ከድሮው ጋር ማወዳደሩ ፡ የሰማይና መሬት ያክል ይራራቃል ቢባል ፡ ማጋነን አይሆንም ፣ ባሁኑ ጊዜ ፡ የሙስሊም ሴቶች ፡ በሚኒስትር ደረጃ ፡ እያየን እንገኛለን ፣ ባለፉት መቶ አመታት ግን ፡ በሙስሊሞቹ ላይ ፡ ቡዙ የተለያየ ጭቆና እንደደረሰባቸው ፡ በማያሻማ ሁኔታ ፡ ሁሉም ሰው ያውቀዋል።
በነ አፄ እብነ ድል ፡ ዘመነ መንግስት ፡ ሙስሊም በቅሎም ሆነ ፈረስ ፡ በኳርቻ መጋለብና ፡ ማነኛውንም የጦር መሳሪያ ፡ መያዝ ለሙስሊሞች በጥብቅ የተከለከለ ነበር ፣ ይሄም አልበቃ ብሎ ፡ አንድት የሙስሊም ቆንጆ ልጃገረድ ፡ ተታየች የዘመኑ ባለስልጣኖች ስለሚቀሟቸው ፡ ዘመዶቿ እንደ ሞተች ቆጥረው ፡ አስቀድመው ልጅ አገረዷ ፡ ተክፍና ይሰገድባትና ፡ ልክርስቲያኖቹ ባለስልጣኖች ፡ ትስጥ ነበር ፣ ይህ ድርጊት ፡ ኢማም አህመድ እስከሚመጣ ድረስ ፡ ሲሰራበት የቆየ ጉዳይ ነው ፣ በተለይ ባአፄ ዩሐንስ ዘመነ መንግስት ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ፡ ሙስሊሞች መኖር አይችሉም ፡ ከኖሩም በግደታ ክርስትና ሀይማኖትን ፡ መቀበል አለባቸው ፡ አልቀበልም የሚል ታለ ፡ በሞት እንደሚቀጣ ፡ በዚሁ ችግር የተነሳ ፡ ተሰላሳ አምስት ሺህ ፡ ሙስሊም በላይ እንደ ተገደለ ፡ አንድ አንድ ታሪክ መዝጋቢዎች ይናገራሉ።
ጌታው ሸህ ሁሴን ጅብሪል ፡ ተወላጅ አባታቸው ጋር ፡ አፄ ዩሐንስ አስጠርተው ፡ ንጉሱ ዘንድ በመቅረብ ፡ አባታቸው የማይቆርቡ ተሆነ ፡ እስከልጃቸው ሞት እንደሚጠብቃቸው ፡ በንጉሱ አንደበት ይነገራቸዋል ፣ የመቶ ሀያ ዓመት ባለቤት ፡ የነበሩት የሸህ ሁሴን ጅበሪል አባት ፡ በሀይማኖታቸው እንደማይደራደእሩ ፡ ለንጉሱ ነገሯቸው ይባላል ፣ አባትና ልጁም ተዛ ችግር ፡ የተረፉ ናቸው ማለት ይቻላል ፣ አፄ ዩሐንስም ፡ ይሄን ሁሉ ግፍ ሰርቶ ፡ በክርስቲያኑ ሕብረተሰብ በኩል ፡ ታላቅ ጅብዱ እንደሰራ ፡ በየ አጋጣሚው ሲመሰገን እናየው አለን ፣ ደግሞ በጣም የሚገርመው ነገር ፡ በዛች ቀውጢ ሰዓት ፡ ይሄን ድርጊት ያስተናገዱትን ፡ የተቃወሙትን በክርክርም ቢሆን ፡ እንድሁም በሚቋጥሯቸ ስንኞች ፡ ጌታው ሽህ ሁሴን ጅብሪል አብራርተዋቸዋል ፣ የፈረዱትን ፍርድ ለጊዜው እንተወውና ፡ እንደ ጋዜጠኛ እንዳንድ ገጣሚ እንኳን ፡ በሙስሊሞቹ በኩል አለመታየታቸው ፡ ምን ያክል የሙስሊሙ ሞራል እንደዋዠቀ ፡ ቁልጭ ባለ መልኩ ያሳየናል።
ያለፉትን የክርስቲያን ባለስልጣኖቸ ፡ ሁሉንም እንደስራችው ስለሚዳስስ ፡ እንድሁም ሌላ ትኩረት በክርስቲያኑ ፡ ሕብረተሰብ ውስጥ የሚያመጣውን ችግር በመረዳት ፡ ሙስሊሞች እየፈራን ፡ ይህ መጻፍ ሳይጻፍ ፡ ለቡዙ አመታት ለንባብ ሳይበቃ ቀርቷል ፣ አሁንም እንኳን ቢሆን የሳቸውን ፍርድ ፡ ክርስቲያን ስለጻፈው ነው እንጅ ፡ አንድ ሙስሊም አስቀድሞ ጽፎት ፡ ቢሆን ኖሮ ፡ ምን ነገር ሊያመጡ ነው ፡ ተብሎ ያ ግለስብ ፡ መድረሻ ያሳጡት ነበር ፣ የት እንደደረሰም ላይታወቅ ይችላል።
ከመጻፉም ውስጥ ፡ በክርስቲያኖቹ በኩል ፡ በዋናነት የሚፈለገው ፓርት ፡ በፓለቲካው ዙሪያ የሚያጠነጥነው ፡ ክፍል ብቻ ሲሆን ፣ ይሄም የሚያሳየን ፡ ጸሀፊውም ቢሆን ሲታገል የምናየው ፡ ያችኑ የፓለቲካዋን ሚስጥር ፡ ያገኘሁ እየመስለው ነው ፣ ስለ አባይ አያነሳም ፡ ሰለተውሂድ አያነሳም ፡ እነዚህን ክፍሎች ፡ ጌታው ሸህ ሁሴን ጅብሪል ፡ አልፈዋል ማለት ፡ በፍጹም የማይታሰብ ነገር ነው ፣ ሙስሊሙ ሕብረተሰብ ፡ መጻፉም ተጁላይ ቢኖር ፡ ለመጻፍም ሆነ ለመናገር ይፈራል ፣ ሙስሊሙ የገዛ ሀይማኖቱን ለማፍረስ ፡ የምን ያክል እስበርሱ ፡ እንደሚፋጅ በየ አጋጣሚው ፡ የምናየው ጉዳይ ስለሆነ ፣ በወቅቱ የሚናገረውን ሰው ፡ ስለሚዘልፉት የለፉትንም አባቶቻችንን ስለሚወቅሱ ፡ እውቀቱ እያለው ፡ ዝምብሎ ጊዜን የጠብቃል።
ያንን መጥፎ ጊዜ ያሳለፉ ፡ ሙስሊሞች ፡ መውሊድ ሶደቃ መንዙማ ወዘተ ፡ እያሉ በመሰብሰብ ፡ እነሆ እስታሁን ድረስ ፡ ሀይማኖቱን ቢያቆዩንም ፡ መመስገናቸው ቀርቶ ፡ ካፊሮች ዘፋኞች አዝማሪዎች ፡ እየተባሉ በየ አጋጣሚው ፡ ሲወገዙ እንሰማለን ፣ ተዚህ በታቸ ፍርዱን ፡ ለናንተ ልተወውና ፡ ወደ ፍርዱ ልመለስ።
ጌታው ሸህ ሁሴን ጅብሪል በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ ያደረሰውን ጭፍጨፋ እንድህ ሲሉ በጊዚያቸው ተናገረውት ሂደዋል።
ዩሐንስ ምን ነካው ፡ ተክለፈለፈሳ እንደስከረ ሰው ፡ አቅሉን እንደረሳ ከቶ ምን ቢሆን ነው ፡ በምን የተነሳ ዩሐንስ ሙስሊሙን ፡ ተዳፈረውእሳ ሺቶበት ነው እንጂ ፡ ታዱንያ ሊነሳ ተሸሺጎም ቢኖር ፡ ምንም ሳይወሳ የሰራሀው ወንጀል ፡ ያሁሉ ፊራሳ ዘላለም ይታያል ፡ የተውከው ጠባሳ የልብ ቁስል ነው ፡ የሳንባ ነቀርሳ ሰው አንቀህ ስትጥል ፡ እንደ በሀር አሳ ምን በደለ እስላሙ ፡ ተምንህ ደረሳ ሰው ይታረዳል ወይ ፡ እንዲሁ ባፈሳ ተቤቱ ተወስዶ ፡ እንዳውሬ እንደ እንስሳ አልተማርን አንጽፍ ፡ ቀለም አናነሳ ተቆርቋሪ የለን ፡ የሚል የት ሄዱሳ ያሰብከውን ሰራህ ፡ የልብህ ደረሳ እጅህ ተነከረ ፡ በደም ተለወሳ መታጠብ አለበት ፡ ያንተው ደምህ ፈሳ ሙስሊሙ እኮ አዘነ ፡ በጣም ተላቀሳ ፈጣሪን ጠየቀው ፡ እንዲከፍለው ካሳ አዛኙ ጌታችን ፡ ሁሉን የማይረሳ ልብህን ገፈፈው ፡ ጦር እንድታነሳ የሰራሀት ስራ ፡ መጣች ተመልሳ ቆራርጣ ልትጥልህ ፡ አንገትክን በጥሳ ጠጅና ስጋህን ፡ ተፊቴ ላይ አንሳ እኔ ለበሬ ሽንጥ ፡ መች ተልቤ ሲሳሳ ባንድ ቀን ተርቤ ፡ ባንድ ቀን አልከሳ አላህ የጠላውን ፡ አልበላም ነጃሳ ወንዝ ለወንዝ ሄጄ ፡ እበላለሁ አሳ ጥጋብህን ቻለው ፡ ቀስ ብለህ አግሳ እያየህ ተራመድ ፡ ለሂወጥ ሳሳ አንገትክን ለማጣት ፡ ምነው ቸኮልክሳ ወይ አንተ አትኖርበት ፡ ወይ ዘርህ አይነግሳ እንድሁ በከንቱ ፡ ትደክማለህእሳ አላህ ነቢይ አድርጎ ፡ ሲልከው ለሙሳ ፊርዐውን ምንድን አለ ፡ ምን ጥያቄ አነሳ? ለምሳሌ ያክል ፡ ትንሿን ብጠቅሳ ያለውን ሰምተሀል ፡ ፈርዐውን ለሙሳ ፈጣሪነኝ ብሎ ፡ ዐላህን የረሳ ጥጋቡን ተመልከት ፡ የት እንደደረሳ ታልገደልኩኝ ብሎ ፡ ሲያባርር ለሙሳ ባህር ቀልጦ ሞተ ፡ ወሬውም ተረሳ ተዋረደ ሞተ ፡ አልቻለም ሊነሳ ፈጣሪ ነኝ ያለው ፡ ሊበላው ነው አሳ እንደት ትሆን ይሆን ፡ ውርደትህ ያንተሳ? እናየው ይሆናል ፡ ያንተም ቀንህ ደርሳ የሙስሊሞቹ ደም ፡ ያኔ ተመለሳ ይሄ ባዱንያ ነው ፡ ያኸይራው ይባሳ ***