ታላቁ የአሏህ(ሱወ) ወልይ ፣ የኮሬቡ አንበሳ ፣ በ1811ዓም ዓም ተወልደው በ1908ዓም በ97 አመታቸው ፣ እዱኒያን የለቀቁት ፣ ጌታው ሸህ ሁሴን ጅብሪል ፣ ትንቢት መናገር የጀመሩት ፣ ገና በ7 አመታቸው ነበር ይባላል። እሳቸው ያልተናገሩት ፣ ያላስገነዘቡት የዘመን መንግስታት ፣ ታሪክም ይሁን ፣ የአለም ስልጣኔ ፣ የለም። ጥልቅ የአማርኛ ቋንቋ ፣ እውቀት ላለው ሰው ፣ የግጥሞቻቸው አነጋገር ፣ በሚያስገርም ሁነታ ፣ ባለ ብዙ ፍቺ ፣ ወይንም ትርጉምን ፣ ያዘሉ በመሆናቸው ፣ እጅጉን ያስገርማሉ። የተናገሩትም ትንቢት መሬት ጠብ እንደማይል ፣ ይወራላቸዋል።
ኦሮሞ ጉራጌ የሸዋ ሙንኪር ሌት እንቅልፍ አይተኙ ቀኑን በነገር ሸዋን ይይዟታል አንድ እንኳ ሳትቀር መሳረያ አስገብተው በድብቅ በሲህር ድንጋዩን በድንጋይ በማነባበር...
እኛ አፈር በገባን በስድሳ አምስት ንጉሥ የተባለ የለውም ሐያት እጁ እየተያዘ ይገባል እሳት ዘሩ እየታደነ እንደ አውሬ እንስሳት ከእኛም ሳይመጣ አይቀር ኋላ ወደፊት...
ለጥቃ ትመጣለች ደግሞ አንዲት ሴት ግዛቷ የሆነ ዘጠኝ አመት አይ አገዛዝ ማማር የዣ ወራት ከዛ የደረሰ አላህ ሽቶለት ዝናም ሐሳብ የለው በበጋው ወራት ጥቂት ከሰብ አርጎ በብዙ ማምረት...
በስተ ፀሀይ መውጫ አለ የሚሉት እኔን የሚመስለኝ የማህመዶች ቤት የአስመራው ባለአባት መሐመድ ደያስ የሚሄድበትም *በለቦላ ፈረስ ያበሻን ዐውሊያ ተራ የሚያደርስ ዐበሻን አድርሶ መቅደላ የሚያደርስ...
ፍርዱን ለማዳመጥ ያላችሁ ጉጉት ሰው ወያኔን ፈርቶ አፉን ዘግቶ አይሞት አአአ*ብዬ ልናገር አፌ ይከፈት እያየህ ተራመድ ልጄ እወቅበት አደራ እንዳታምነው ወገን ጎረቤት
ሁሉም አለው ጊዜ ሁሉም አለው ወቅት ወያኔም ሲያበቃ አለው ምልክት መሳሪያ ያበዛል የጦር ሰራዊት በመኪና ሚጫን የሚያዝ በእንግት ምን መላ ይገኛል ጦር ቢያከማቹት...
አለህም እንዳልል ስፍራህን ማን ያውቃል? የለህም እንዳልል ይመሻል ይነጋል እንዴት ያንተን ስፍራ ሸይጣን ይደፍረዋል? ወትሮም ጥበብ ሰሪ ሰው ያስወነጅልካል ያልሆነውን ሆነ እያለ ያወራል...
እኛ አፈር በገባን በአንድ መቶ ዓመት ተፈሪ ዓይኑን ታሞ ይገባል መሬት ማር የላሰ ሁሉ ይቀምሳል እሬት የበላውም አይቀር ሽቅብ ሲያስተፉት ካለው ይገድሉታል ለገዘብ ስስት...
የአላህን ትተው በውሻ የሚመሩ በሐበሻ መሬት ግፍን የሚሠሩ ቁመታቸው አጭር መልካቸው የሚያምሩ አይነግሡም ብላችሁ አትወዳደሩ ሃምሳ ዓመት ይነግሣል እግረ ውትርትሩ...
ማረዱ ከፋ እንጂ ጀግንነት አያጣም እስላምን ሚያርድ እንጂ የሚወድ አይመጣም የፈራ ሰው ይውጣ እኔ መልስ አላጣም ይዘገያል እንጂ ሰው የጁን አያጣም መተማ ከሄደ ተመልሶ አይመጣም...